ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከጃንዋሪ, 2014 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ያላለቀ ድርሰት

ያላለቀ ድርሰት Written by   አንተነህ ይግዛው       “ኧረ ይብቃህ ደጀኔ!... አራት ሰዓት ሞላኮ!...” አሉ እትየ ስንዱ፣ መጋረጃውን ገለጥ አድርገው ከወደ ጓዳ ብቅ እያሉ፡፡ “አንቺ ግን ለምን ሰላም አትሰጪኝም!?...” ደጀኔ አቀርቅሮ ከሚጽፍበት ቀና በማለት በንዴት ጦፎ እስክርቢቶውን ወረወረ፡፡ “ስንቴ ልንገርሽ አክስቴ!?… በውስጤ የታመቀውን የደራሲነት ስሜት መተንፈስ እንጂ፣ የኮሌጅ ትምህርት አጠናቆ መመረቅ አይደለም የህይወቴ ጥሪ!” እየተንቀጠቀጠ ተናገረ፡፡ “የዛሬውስ የተለየ ነው!... ገና በማለዳ ንትርክ ጀመራችሁ?” የእማማ በለጡ ድምጽ በስተቀኝ ያለውን የኮምፔርሳቶ ግድግዳ አልፎ ተሰማ፡፡ ከጉዳይ የጣፋቸው አልነበረም፡፡ “ተው እንጂ ደጀኔ… ደህና ሂደህ ሂደህ አንድ አመት ሲቀርህ አትሰላች!” በትህትና መለሱለት፡፡ “አንቺኮ ችግርሽ ይሄ ነው!... የጀመርኩትን ትምህርት እንጂ፣ የጀመርኩትን ድርሰት ስለመጨረሴ አትጨነቂም!” ከተቀመጠበት ብድግ አለ፡፡ ሁለት አንቀጽ ጅምር አጭር ልቦለድ የጻፈባትን ወረቀት ከጠረጴዛው አንስቶ በፍጥነት ወደ ጓዳ አመራ፡፡ “እኔኮ ላንተ ብየ ነው!... ደሞም’ኮ አትጣፍ አላልኩህም፡፡ ከኮሌጅ ስትመለስ መጨረስ ትችላለህ” አሉት አክስቱ በትህትና ፈገግ ብለው፡፡ የአክስቱ ትህትና የገነፈለ ስሜቱን በረድ አደረገለት፡፡ እንደወትሮው አልተቆጡትም፡፡ እንደሌላው ጊዜ ልብ የሚሰብር ነገር አልተናገሩትም፡፡ “ደሞ አንተን ብሎ ደራሲ!... የአስር ሳንቲም ሻይ ቅጠል የማይገዛ እንቶፈንቶ መሞንጨሩን ትተህ፣ ትምህርትህን ብታጠና ይሻልሃል!” ብለው አልተሳለቁበትም፡፡ ወደ ጓዳ የጀመረውን ...